አውስትራሊያ፤ በጋዛ በንጹሃን ዜጎች ላይ እየተፈጠመ ነው ያለችውን ግድያ አወገዘች።

የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔኒ ዎንግ በቅርቡ እስራኤል በጋዛ ላይ በደረሰ ጥቃት የንጹሃን ዜጎችን ሞት ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

ዎንግ የትኛዎቹን ጥቃቶች እየጠቀሱ እንደሆነ ባይገልፅም ነገር ግን ብዙዎቹ ትምህርት ቤቶች አቅራቢያ እንደሆኑ ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ በጋዛ ለመጠለያነት የሚያገለግሉ ስምንት ትምህርት ቤቶች ጥቃት ደርሶባቸዋል ብሏል።

አውስትራሊያ ለስምንት ወራት ያህል የተኩስ አቁም ጥሪ ስታቀርብ ቆይታለች ሲሉም ዎንግ በኤክስ ገፃቸው ላይ መፃፈቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

በሐመረ ፍሬው
ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *