በቀይ ባህር ላይ በሚሰነዘሩ ጥቃቶች ምክንያት የስዊዝ ካናል አመታዊ ገቢ ቅናሽ አሳይቷል ተባለ፡፡

በ2023-24 የሒሳብ ዓመት የተገኘው ገቢ ከ9.4 ቢሊዮን ዶላር ወደ 7.2 ቢሊዮን ዶላር ዝቅ ማለቱን የግብፅ የካናል ባለስልጣን ገልጿል።

ላኪዎች በቀይ ባህር ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃት የተነሳ ካናሉን የሚጠቀሙ መርከቦች ቁጥር ከ25,911 ወደ 20,148 ዝቅ ብሏል።

ከህዳር ወር ጀምሮ ሁቲዎች የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ሃማስ ከእስራኤል ጋር በሚያደርገው ውጊያ ድጋፍ ለማሳየት በቀይ ባህር እና በህንድ ውቅያኖስ የንግድ መርከቦችን እያጠቁ ነው።

ለግብፅ ቁልፍ የዉጭ ምንዛሬ ምንጭ የሆነዉ ሲዊዝ ካናል ባለስልጣናቱ ገቢዉን ለማሳደግ እየሞከሩ መሆኑን ገልፀዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በቁምነገር አየለ

ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *