በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ አሞ እና ኤሪ ዞኖች ሀገረ-ስብከት ለከፍተኛ የሰባዊ ቀዉስ ለተዳረጉ ወገኖች ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቀረበ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ አሞ ና ኤሪ ዞኖች ሀገረ-ስብከት ፤ በሀገር ስብከቱ ለሚሠሩ መንፈሳዊ፣ ማሀበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ሥራዎችን አስመልክቶ በዛሬው እለት መግለጫ ተሰጥቷል ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብ አሞና ኤሪ ዞኖች ሀገረ-ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ፤ አሁን ላይ የአከባቢው ነዋሪዎች በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ ችግር ውስጥ ናቸው ብለዋል።

ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ በአከባቢው ለዓመታት በዘለቀውን የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት በአከባቢው መሰረተ ልማት ባለመኖሩ በእጅጉ እየተጎዱ ይገኛሉ ነዉ ያሉት፡፡

በተጨማሪም በተፈጥሮ ድርቅ እና ጎርፍ በረሃብ፣በእርዛት ፣በበሽታ ተጠቅተው ይገኛሉ ብለውናል ።

ብፁእነታቸው “የሰው ልጅ ሆይ ወደ ደቡብ አቅና” በሚል መሪ ሐሳብ አከባቢውን እና የአከባቢውን ነዋሪዎች በመንፈሳዊ፣በማህበራዊ እና በኢኮኖሚያዊ ለመደገፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮጀክት መዘጋጀቱን ነግረውናል።

ይህ የድጋፍ ጥሪ ከሐምሌ 15 እስከ ነሐሴ 30 ድረስ የሚቆይ ነው ተብሏል።

በመሆኑ ማንኛውም ምእመን በከፍተኛ ችግር ውስጥ ለሚገኙት የአከባቢው ነዎሪዎች ለመስራት ለታለመው የትምህርት ቤት፣ሃኪም ቤት፣ፋርማሲ እንዲሁም የግብርና ልማት ስራ ሁሉም እጁን እንዲዘረጋ ተጠይቋል ።

እነዚህ የልማት ስራዎች የሚሰሩት በሶስት ዞኖች ነው የተባለ ሲሆን እነሱም በጅንካ፣በአሪና በኦሞዞን ዞን ነው ተብሏል ።

በመሆኑ ሁሉም በየአቅሙ ትብብር እንዲያደርግ የ100 ብር ፣የ250 ብር፣ የ500 ብር እና የ1000 ሺህ ብር ዋጋ ያላቸውን ፤ 1 መቶ ሺህ ትኬቶች በአዲ አበባ በሚገኙ ገዳማት አጥቢያ ቤተክርሲቲያን ፣ማህበራትና የንግድ ተቋማት ተሰራጭቷል ብለውናል።

ከዚህ ባለፈ ሁሉም ምዕመናን ተሳታፊ ለማድረግ የክፍያ አማራጮችን በመጠቀም በአሃዱ ባንክ እና የበይነመረብ የገቢ መሰብሰቢያ መተግበሪያ መዘጋጀቱንም ነግረውናል ።

እነዚህ ትኬቶች እና መተግበሪያው ከሃምሌ 15 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ ይፋ ይሆናል ብለዋል።

በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በ/ክርስቲያን አገልጋዮች፣ ካህናትና ምእመናንን የበኩላቹን በመወጣት ከቤተክርስቲያን ጎን እንድትቆሙ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ልዑል ወልዴ

ሐምሌ12 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *