በግሪክ የባህር ላይ ጠባቂዎች ወደ ቱርክ ወንዝ የተገፈተሩ ስደተኞችን ማዳኗን ቱርክ ገለጸች፡፡

ወደ ግሪክ ሊገቡ የነበሩ ስደተኞችን ይዛ የነበረችን ጀልባ የግሪክ የባህር ላይ ጠባቂዎች ወደ ቱርክ ወንዝ ገፍተረዉ ሲመልሷት በወታደራዊ ድሮኖች እገዛ ታይቷል፡፡

ሰዉ አልባ በሆነ ድሮን እገዛ የታየዉ ምስል የግሪክ የባህር ላይ ጠባቂዎች ጀልባዋን ገፍትረዉ ወደ ወንዙ ከመለሷት በኋላ ስፍራዉን ለቀዉ ሲሄዱ ነዉ፡፡

እንደ ቱርክ ብሄራዊ መከላከያ ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ ፤ ጉዳዩ የደረሳቸዉ የቱርክ የባህር ላይ ጠባቂዎች በፍጥነት ወደ ስፍራዉ በመሄድ ስደተኞቹን ለመታደግ ችለዋል፡፡

ቱርክ ወደ አዉሮፓ በማቅናት አዲስ ህይወት መጀመር ለሚፈልጉ በተለይም ጦርነት እና መከራን በመሸሽ ወደ አገሯ
ለሚገቡ ጥገኝነት ጠያቂዎች ዋና የመሸጋገሪያ ቦታ መሆኗ ይገለጻል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *