በአማራ ክልል 34 ወረዳዎች በአስጊ የወባ ወረርሽኝ ስርጭት ላይ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
የወባ ወረርሽኙን ለመግታት ከፍተኛ የሆነ ሁሉን አቀፍ ንቅናቄ መፍጠር ካልተቻለ ማህበረሰቡን የሚያጠቃበት ደረጃ ላይ መድረሱም ተገልጿል፡፡
ስለሆነም ማህበረሰባዊ ንቅናቄ በበመፍጠር ከወባ ወረርሽኙ የአካባቢውን ማህበረሰብ መታደግ እንደሚገባ ተጠቅሷል፡፡
የጤና ልማትና ጸረ ወባ ማህበራት በበርካታ ወረዳዎችና ቀበሌዎች የመከላከል ሥራ እያከነወኑ ቢሆንም ተጨማሪ ጉልበትና ተባባሪ ሃይል እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ሃላፊነት በመውሰድ የዩኒቨርሲቲውንና የአካባቢውን ማሕበረሰብ ከወባ ወረርሽኝ ለመጠበቅ አስቸኳይ ስራ እንዲጀምር አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
በተጨማሪም የከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያዎች፣ የክልል ጤና ቢሮ እና ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጋራ የወባ ወረርሽኝ ምላሽ እንዲሰጡ ትዕዛዝ መተላለፉን የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም
