በአካባቢው ግጭት በመፍጠር ተጠርጥረው በፍርድ ቤት ትእዛዝ የወጣባቸው የህግ ተፈላጊዎች አሁንም በህዝቡ መሃል ችግር ለመፍጠር ጥረት እያደረጉ ናቸውም ተብሏል።
ባለፈው 2016 በጀት አመት ክልሉ ተረጋግቶ እንዳይቀጥል ለማድረግ ሲደረጉ የነበሩ የወንጀል ድርጊቶችን በመቆጣጠር አንጻራዊ ሰላም ማምጣት እንደተቻለ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳ እንዳሉት፣ በበጀት አመቱ የማህበራዊ ሚዲያ ሃሰተኛ መረጃዎች፣ የሀይማኖትና የብሄር ግጭት ቅስቀሳዎች በስፋት መስተዋላቸውን ተናግረዋል።
የክልሉ ፖሊስ ሀሰተኛ መረጃዎችንና በሃይል የተደገፉ የመዋቅር ጥያቄዎችን በመቆጣጠር የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ማድረጉንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ኮሚሽኑ የፖሊስ ማሰልጠኛ ማዕከላትን በመገንባት የፖሊስ አባላትን አቅም መገንባት ላይ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም
