የጎፋ ዞን አደጋ ስጋት ስራ አመራር ሃላፊ አቶ ማርቆስ መለሰ በተከሰተዉ የሟቾች ቁጥር ከ2መቶ 20 በላይ መድረሱን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
አብዛኞቹ ሟቾች በአንድ የቤተሰብ አባላት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ እነሱን ለማትረፍ እና ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ለነብስ አድን ሥራ ወደ ስፍራው ያቀኑ መሆናቸዉንም አስታዉቀዋል፡፡
በአደጋው ለነብስ አድን ሥራ ቀድመው በስፍራው የተገኙ የቀበሌውን አስተዳዳሪ ጨምሮ መምህራን፣ የጤና ባለሞያዎች እና የግብርና ባለሞያወች የአደጋው ሰለባ ሆነዋል።
አስክሬን የማፈላለጉ ስራዉ ተጠናክሮ እንደቀጠለና የፌደራሉ መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አባቱ መረቀ
ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም
