የባንግላዴሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼይክ ሃሲና ተቃዉሞዉ መበርታቱን ተከትሎ ስልጣናቸዉን ለቀዉ አገር ጥለዉ መሰደዳቸዉ ተሰምቷል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሯ መንግስትን በመቃወም ከስልጣን ይልቀቁ በሚል በተደረገ ሰልፍ ብዙዎች በተገደሉበት ማግስት አገር ለቀዉ መጥፋታቸዉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡
ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ጠቅላይ ሚኒስትሯ እና እህታቸዉ በጦሩ ሂሊኮፕተር ተጭነዉ ለደህንነታቸዉ ሰላም ወደ ሆነበት ስፍራ መሄዳቸዉ ሲገለጽ፤ ያሉበት ቦታ ግን ግልጽ አልተደረገም፡፡
ወደ ህንድ ሊያመሩ ይችላሉ የሚሉ መላምቶች ግን መኖራቸዉ ተገልጿል፡፡
በአገሪቱ ተግባራዊ ይደረጋል በተባለው የስራ ኮታ ምክንያት የተቀጣጠለው ተቃውሞ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ስልጣን እንዲለቁ ወደ መጠየቅ ተዘዋውሯል።
በትናንትናዉ ዕለትም ጠቅላይ ሚኒስትር ሼይክ ሃሲና ስልጣን እንዲለቁ በማለት ዳግም ወደ አደባባይ የወጡ 91 ሰዎች ሲገደሉ 13ቱ የፖሊስ መኮንኖች መሆናቸው እና ብዙዎች መቁሰላቸው ተገልጿል።
ሰልፈኞቹ በሐምሌ መጀመሪያ ላይ ተማሪዎች የስራ ኮታን በመቃወም የጀመሩትን ሰልፍ በማቀጣጠል ለ2 አስርት ዓመታት በስልጣን ላይ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትሯ ስልጣን ይልቀቁ ወደሚል ጥያቄ አሸጋግረውታል።
በዚህም እስካሁን በአጠቃላይ ህይወታቸዉ ያለፉ ሰዎች ቁጥር ከ3መቶ መብለጡን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም
