በፍትሐብሄር እና በወንጀለኛ መቅጫ ላይ የሚገኙት እነዚህ ሕጎች ከ50 አመት በላይ አድሜንም አስቆጥረዋል፡፡
በጎንደር ዩንቨተርስቲ የህግ መምህር እና ጠበቃ የሆኑት ዮሴፍ ወርቀልኡል ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ህግ በተፈጥሮው ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ ተደርጎ የሚሰራ እንደሆነ ገልጠው ነገር ግን መሻሻል የሚገባቸው ህግች ግን መሻሻል እንዳለባቸው ጠቅሰውልናል፡፡
ሌላኛው የህግ አማካሪ እና ጠበቃ አቶ ባዩ ጥላሁንም በኢትዮጵያ መሻሻል ያለባቸው ህጎች በስፋት እንዳሉ አንስተው ከነዛ ውስጥም የካሳ ህግ ዋነኛው እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
ባለሞያው እንዳለቱም የካሳ ሀግ በ1950ዎቹ አካባቢ የወጣ እና እስካሁን ያልተሸሻለ መሆኑን አንስተው አሁንም ለሞራል ካሳ ክፍያው ከአንድ ሺ ብር እንደማይበልጥም ተናግረዋል።
በሌላ በኢትዮጵያም ከዘመኑ ጋር የማይሄዱ እና ከፀደቁ ረጅም ዓመታት ያስቆጠሩ ሕጎች ተብለው በባለሞያዎቹ ከተነሱት ህጎች መካከልም የወንጀለኛ መቅጫ ህጉ አንዱ እንደሆነ ባለሞያው ገልጠዋል።
ዘመናዊ የህግ ስረዓት ከተጀመረበት ከቀዳሚዊ ሀይለ ስላሴ ዘመነ መንሰግት 1950 ዎቹ ጀምሮ የፍታብሄር የወንጀል የፍታብሄ ስነስርዓት እና የቤተሰብ መምሪያ ህፎች ያሏት ሲሆን መቀየር እያለባቸው ሳይቀየሩ ብዙ የቆዩ እነዳሉም ተነግሯል ።
በዚኅም የውርስ እንዲሁም የካሳ ወነጀለኛ መቅጫ ህጎችም መሻሻል እያለባቸው ሳይሻሻሉ በመቅረታቸው ዳኞች ለተለያዩ ውሳኔዎች እነድሚዳረጉም ተነስቷል፡፡
የህግ ባለሞያው ጠበቃ ባዬ ጥላሁንም በዚህም ምክንያት ለተመሳሳይ ወንጀል የተለያየ ፍርድ ሊሰጥ የሚችልበት ሂደት እንደሚፈጠርም ተናግረዋል፡፡
ለአለም አሰፋ
ነሃሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም
