የመቀሌ  ዩንቨርስቲ  መምህራን   ጥያቄያችን ምላሽ ተነፍጎታል አሉ፡፡

መምህራኑ   የሚከፈላቸው ደሞዝ  እና  የኑሮ ውድነት  ባለመመጣጠኑ ምክንያት አሁንም  ችግር ላይ መውደቃቸወን ገልጸዋል፡፡

ከጦርቱ  ጋር በተያያዘ  ከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቀናል የሚሉት መምህራኖቹ የ17 ወር ደምወዝ እስካሁን እንዳልተከፈላቸው እና አሁን ላይ የሚከፈላቸው የወር ደሞዝ እና የኑሮ ውድነቱ ሊጣጣም አለመቻሉን ከጣቢያችን ጋር  በነበራቸው ቁይታ ተናግረዋል፡፡

መምህራኖቹ ሁሉም የፌደራል እና የክልል የስራ ሀላፊዎች  አስቸኳይ ምላሽ እና  ድጋፍ በማድረግ ዩንቨርስቲው ወደ ቀድሞ የመማር ማስተማር ስርአቱ እንዲገባ ቢያደርጉ  ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የመቀሌ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳነት ዶክተር ተካቡ ገብረስላሴ በበኩላቸው  ችግሩ  ስር መስደዱን አንስተው መንግስትም ይሁን የክልሉ የሚመለከታቸው አካላት አሰቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በኑሮ ውድነቱ ምክንያት መምህራኑ ችግር ላይ መውደቃቸውን ጣቢያችን መዘገቡ ይታወሳል፡፡

በሊዲያ ደሳለኝ

ነሃሴ 2 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *