በአዲስ አበባ ከተማ እየተጠናቀቀ በሚገኝው 2016 አመት 70 አዳዲስ የፓርኪንግ ማህበራት መደራጀታቸው ተነግሯል።

በነዚህ 70 በሚሆኑ ማህበራት ውስጥ 1ሺህ 900 ለሚጠጉ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር እንደተቻለም ነው የተነገረው።

እነዚህ የፓርኪንግ ቦታዎች የሚያዘጋጀው እና የፓርኪንግ ማህበራት የሚያደራጀው የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመት ባለስልጣን ነው።

የባለስልጣኑ የህዝብ ግኑኝነት እና የዲጂታል ሚዲያ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ መኳንንት ምናሴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ በመዲናዋ የትራፊክ ፍሰቱን ጤናማ ለማድረግ አዳዲስ የፓርኪንግ ቦታዎች እየተዘጋጁ ይገኛሉ።

በከተማው በአጠቃላይ 275 የሚሆኑ የፓርኪንግ ማህበራት መኖራቸውን የተናገሩት ባለሙያው፣ ማህበራቱ ጠንካራ እንዲሆኑ የተለያዩ ድጋፎች እየተደረገላቸው ይገኛልም ብለዋል።
የፓርኪንግ ቦታዎች ደህንነታቸው የተረጋገጠ እንዲሆን በቀጣይ በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ነሐሴ 06 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *