የግሪን ዌቭ አልያንስ ድርጅት መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሚኪ ነጋሳ፤ ድርጅታቸው ባለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር ችግኝ መትከሉን አስታዉሰዋል፡፡
የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች፣ አትሌቶች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ባለሀብቶች፣ አባ ገዳዎች እና ሃዳ ሲንቄዎች ፤ የማኀበራዊ ሚዲያ አንቂዎች የተሳተፉበትን የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር ማዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡
አቶ ሚኪ የተጀመረዉ ተግባር ለአለም የተረጋጋ የአየር ንብረት እንዲኖር እና ለፍጥረታት የሚያበረክተዉ አስተዋፅ እጅግ ጉልህ በመሆኑ አንዴ ተክለን የምናቆመዉ ሳይሆን በቀጣይነት የምንሰራዉ ስራ ነዉ ብለዋል፡፡
በዚህም በዘንድሮዉ ለ4ኛ ጊዜ በተካሄደዉ የችግን ተከላ መረሃግብር ከ10 ሺህ በላይ ችግኞች መተከላቸው ነግረዉናል።
በአካባቢ ጥበቃና እንክብካቤ ላይ የሚሰራው ግሪን ዌቭ አልያንስ የተሰኘው ሀገር በቀል ግብረ ሰናይ ድርጅት የምትተክል አገር የሚያፀና በሚል መሪ ቃል ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማድርገ ስራን በመተግበር ላይ እገኛለሁ ብሏል፡፡
በልዑል ወልዴ
ነሐሴ 06 ቀን 2016 ዓ.ም
