የክረምት ድባቴ

ክረምት ሰውነታችን ጥሩ እንዲሰማው የሚያደርጉትን ስሜቶች እንዲጠፉ እንደሚያደርግ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

በክረምት ስለሚከሰት የድባቴ ስሜት እንዲነግሩንም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ልቦና አስተማሪ እና ተባባሪ ፕሮፌሰር ከሆኑት ዶ/ር በላይ ሀጎስ ጋር ጣቢያችን ቆይታ አድርጓል፡፡

የክረምት ድባቴ በምን ይከሰታል ?

ክረምት ከስነልቦና አንፃር ከስሜት መቀያየር ጋር ይያያዛል ይላሉ፡፡

ክረምት ማለት የፀሀይ ብርሀን የሚቀንስበት ዝናብ እና ቅዝቃዜ ያለበት ወቅት ስለሆነ ቀደም ካለው አየር ሁኔታው ሲቀየር ስሜታችንም አብሮ እነደሚቀየር ይናገራሉ ፡፡

አብዛኛውን ጊዜ ክረምት ከመደበት ፣ እንቅስቃሴ ከመቀነስ እና ደስተኛ ካለመሆን ጋር ይያያዛል ፡፡

በክረምት የጭለማው መብዛት የድባቴው ስሜት እንዲመጣ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡

ይህም የሚፈጠረው ጭንቅላታችን ስሜቶችን የሚያስተናግደው አዕምሯችን ውስጥ በሚፈጠር ኬሚካል ስለሆነ ነው ፡፡

ጨለምለም ሲልም ’’ሜላቶኒን’’ የተባለ ሆርሞን በብዛት ይመረትና ድካም ድካም የማለት፣ እንቅልፍ የመፈለግ እና ለመንቀሳቀስ አለመፈለግ ይፈጠራል፡፡

የድባቴ ስሜቱ የሚመጣበት ዋናው ምክንያትም የፀሀይ ብርሀን በመቀነሱ እና ጨለማ በመጨመሩ ምክንያት ሆርሞኑ በአብዛኛው በመመረቱ መሆኑን ያነሳሉ ፡፡

የሚያመጣው ተፅዕኖ ምንድን ነው?

  • የምንሰራውን ስራ ለመስራት መቸገር
  • መንቀሳቀስ አለመፈለግ
  • ምንም ነገር ለማድረግ ፍቃደኛ አለመሆንን ሊያስከትል ይችላል፡፡

እንዴት መከላከል እንችላለን ?

  • አስተሳሰባችንን ማስተካከል
  • ስራ ለመስራት መሞከር
  • የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ማድረግ
  • ያለንበት አካባቢ በበቂ ሁኔታ ብርሀን እንዲኖረው ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

በመጨረሻም በክረምት ወቅት የሚከሰት ድባቴን ለማስወገድ ስሜቱን በማሸነፍ ለመንቀሳቀስ መሞከር እንደሚመከር ዶ/ር በላይ ተናግረዋል፡፡

በሐመረ ፍሬው

ነሐሴ 06 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *