የቪዛ ዳይሬክት አገልግሎት በተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚኖሩ የቪዛ ካርድ ተጠቃሚዎች የቴሌብር ቨርችዋል ካርድ ቁጥርን ብቻ በመጠቀም ገንዘብ ወደ ሀገርቤት ለማስተላለፍ የሚያስችላቸው ነዉ ተብሏል።
ኢትዩ ቴሌኮም ደንበኞች የዋሌት ቨርቹዋል የቪዛ ካርድ እንዲኖራቸው የሚያስችል እንዲሁም ነባሩን የሃዋላ አገልግሎት በእጅጉ የሚያዘምኑ ቪዛ ዳይሬክት እና ቴሌብር ሬሚት የተሰኙ የአለም አቀፍ ገንዘብ ማስተላለፊያ ሀዋላ አገልግሎቶችን ለማቅረብ የሚያስችል ስትራቴጂያዊ የአጋርነት ስምምነት ከዓለም አቀፉ አንጋፋ የቪዛ ኩባንያ ጋር በትናንትናዉ እለት ፈጽሟል፡፡
በተመሳሳይ ቴሌ ብር ሬሚት አገልግሎት ደንበኞች የቴሌብር ሞባይል ቁጥራቸውን ብቻ በማጋራት ከዘጠኝ ሀገራት ማለትም አሜሪካ፣ካናዳ፣ እስራኤል፣ሳኡዲአረቢያ፣ ዩናይትድ አረብኢምሬትስ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ጣሊያን እና ስዊድን ገንዘብ በሃዋላ መቀበል እንደሚቻል ተገልፆል።
ይህ ስምምነት ደንበኞች የቨርችዋል ቪዛ ካርድ ቁጥር እንዲያገኙ እንዲሁም ከመደበኛው ሃዋላ የተሻለ አማራጮች ለማቅረብ መሆኑን ተነግሯል።
ይህ አገልግሎት ድንበር ተሻጋሪ ክፍያዎችን ኢ-ኮሜርስን ጨምሮ በኦንላይን በቀላሉ መፈጸም በማስቻል የዲጂታል ፋይናንስ ሥነምህዳር ተደራሽነትን ያሰፋል ተብሏል
በቁምነገር አየለ
