ከተላከ ከ1መቶ21 ዓመት በኋላ የደረሰዉ ፖስት ካርድ

ከተላከ ከ1መቶ21 ዓመታት በኋላ ወደተላከበት አድራሻ የደረሰዉ ፖስት ካርድ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

የስዋንሲ ህንጻ ማህበረሰብ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ላይ እንዳሰፈረዉ ዓርብ ዕለት ለዚሁ ሰፈር አድራሻ እና የቤት ቁጥር የተላከ ፖስት ካርድ ከ1መቶ21 ዓመታት በኋላ ደርሷል፡፡

ፖስት ካርዱ ሊድያ ዴቪስ ለተባለች ሴት የተላከ ሲሆን፤ስፍራዉ ባንክ ከመሆኑ በፊት ትኖር የነበረች ሴት እንደምትሆን ተገምቷል፡፡

የባንኩ የማርኬቲንግ እና ኮሚኒኬሽን ኦፌሰር የሆኑት ሄነሪ ዳርቢ፤ አድራሻዉ ትክክል ነዉ ፡፡ አሁንም 11 እና 12 የሰፈር ቁጥር ነዉ ያለን ነገርግን ፖስት ካርዱ መድረስ ከነበረበት ጊዜ 1መቶ21 ዓመታት ዘግይቷል ሲሉ ለዌልስ ኦንላይን ተናግረዋል፡፡

“በእርግጥ ግር ይላል፡፡ትንሽ የሚያስደነግጥም ነገር አለዉ፡፡ማህተሙ ራሱ የንጉስ ኤድዋርድ ነው፣ ስለዚህ እሳቸዉ ከ1901 እስከ 1910 ንጉስ ነበሩ፣ እና ከእጅ ጽሁፋቸዉ እና አነጋገር በቀጥታ እርሳቸዉ እንደነበሩ መረዳት ይቻላል፡፡ ሲሉ ገልጸዋል፡፡

‹‹ውዴ አልቻልኩም፡፡በጣም ብዙ ጊዜ ሞክሬ ነበር” የምትል አጭር መልዕክትም በፖስት ካርዷ ላይ ተጽፋለች፡፡

በፖስት ካርዱ ላይ ከተጻፈዉ ብዙዉን ነገር ለማንበብ አሁን ላይ በጣም ያስቸግራል ነገርግን የተጻፈዉ በነሀሴ 3 1903 እንደነበር ለማወቅ ተችሏል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የሮያል ሜል ቃል አቀባይ የሆኑት ግለሰብ ከፖስት ካርዱ ዘመናትን ዘግይቶ መድረስ ጀርባ ያለዉ ታሪክ ግልጽ አይደለም ብለዋል፡፡

አንድ መልዕክት ወደ ሲስተማችን ከገባ በኋላ ወደ ትክክለኛዉ አድራሻ የመላክ ግዴታ ስላለብን ፖስት ካርዱ ወደ ሲስተም ከገባ በኋላ ተመልሶ ይሆናል እንጂ ጠፍቶ የቆየ አይመስለኝም ሲሉ ቃል አቀባይዋ መግለጻቸዉን ዩፒአይ ዘግቧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ነሐሴ 14 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *