በኢራን  በመኪና አደጋ የ28 ሰዎች ህይወት አለፈ ።

ፓኪስታናዊ ሀጃጆችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ ተገልብጦ በትንሹ 28 መንገደኞች መሞታቸውን የኢራን መንግስት ሚዲያ ዘግቧል።

አደጋው የደረሰው ማክሰኞ ምሽት በማዕከላዊ ኢራን ያዝድ ግዛት ሲሆን፤በተበላሸ የፍሬን ሲስተም መሆኑን ሮይተርስ  አስነብቧል፡፡

በተጨማሪም ሌሎች 23 ተሳፋሪዎች መቁሰላቸውንና 14ቱ ደግሞ ከባድ አደጋ  እንደደረሰባቸዉ በኢራን የፓኪስታን አምባሳደር መሀመድ ሙዳሲር ቲፑ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ተጓዦቹ ከፓኪስታን ሲንድ ግዛት ወደ ኢራቅ ቅድስት ከተማ ካርባላ እየተጓዙ እንደነበርና፤በሺዓ አቆጣጠር ውስጥ ካሉት ታላላቅ ክስተቶች መካከል አንዱን ለማክበር ሲጓዙ የነበሩ መሆናቸዉ ተገልጿል፡፡

በአደጋው ወቅት ከላርካና፣ ጎትኪ እንዲሁም ሲንድ ከተሞች የተዉጣጡ ወደ 50 የሚጠጉ የሃይማኖት ተጓዦች በአውቶቡሱ ውስጥ እንደነበሩ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡

በአደጋው ህይወታቸዉ ያለፈዉ  11 ሴቶች እና 17 ወንዶች መሆናቸዉን የአደጋ ስጋት አስተዳደር ዳይሬክተር አሊ ማሌክዛዴህ ተናግረዋል።

አውቶቡሱ ከዋና ከተማይቱ ቴህራን በስተደቡብ 681 ኪሜ ርቀት ላይ በሚገኘው በኢራን ዲህሺር-ታፍት የፍተሻ ጣቢያ ፊት ለፊት መቃጠሉን የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *