ኢትዮጵያ ከስድስት ዓመት በኋላ የሴት ልጅ ግርዛትና ያለ እድሜ ጋብቻን ሙሉ ለሙሉ ለማስቆም እንደምትሰራ ተገለፀ

ሀገሪቱ የሴት ልጅ ግርዛትና ያለ እድሜ ጋብቻን ሙሉ ለሙሉ ለማስቆም ለቀጣይ አመት አሳካለው ብላ የነበረች ቢሆንም ስር በሰደደው ማሕበራዊ ወግ፣ የተዛባ የስርአተ ጾታ ግንኙነትና ባለፉት አምስት ዓመታት በገጠማት የኮሮና በሽታና የጸጥታ ችግሮች ልታሳካ እንዳልቻለች የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ ገልፀዋል።

አንዳንድ የቅርብ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በኢትዮጵያ እድሜያቸው 18 ካልሞሉ ሴቶች መሀል ከአስሩ አራቱ ያለ እድሜ ጋብቻ ይፈጽማሉ ።

ሚኒስትሯ ኤርጎጌ ተስፋዬ “ምንም እንኳን ጥረታችን ፍሬ አፍርቶ ውጤቱን በተጨባጭ ማየት መጀመራች የሚታመን ቢሆንም ዛሬም ችግሩ ሙሉ በሙሉ አለመወገዱ ገሃዳዊ እውነታው ከእናንተ የተሰወረ አይደለም።

የተናጠል ጥረታችንና ቁርጠኝነታችን በሚፈለገው ደረጃ ከፍ ባለማለቱ የተነሳ ልጆቻችን አሁንም የጎጂ ልማዳዊ ድርጊትና የጥቃት ሰለባ እየሆኑ ይገኛል” ብለዋል።

በቀጣይ ስድስት ዓመት ይሄን ችግር ሙሉ ለሙሉ መለቅረፍ ሀገሪቷ ማቀዷን ገልፀው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ይሄን የበኩላቸውን ድርሻ ይሄን ዕቅድ ለማሳካት እንዲረባረቡ ጠይቀዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *