በጋዛ የሟቾች ቁጥር መጨመሩ ተገለፀ፡፡ By Ethio AdminAugust 22, 2024የውጭ ዜና ከጥቅምት 7 ጀምሮ በእስራኤል ወታደራዊ ጥቃት ቢያንስ 40 ሺ 2 መቶ 65 ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል፡፡ እንዲሁም 93ሺ 1 መቶ 44 ሰዎች መቁሰላቸውን የአከባቢው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቋል። ከነዚህ ውስጥ ባለፉት 24 ሰአታት 42 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ 163 ቆስለዋል ሲል ሚኒስቴሩ አክሎ ገልጿል። በሐመረ ፍሬውነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም