ሄዝቦላህ በጎላን ተራራማ ቦታዎች ላይ የሮኬት ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ፡፡

እስራኤል በሊባኖስ ጥቃቷን አጠናክራ መቀጠሏን ተከትሎ ሄዝቦላህ ጥቃት መፈጸሙ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ሄዝቦላህ በጎላን ተራራማ ቦታዎች ላይ ያደረሰዉን የሮኬት ጥቃት ተከትሎም በስፍራዉ ሁሉን አቀፍ ጦርነት እንዳይጀመር ፍራቻ መጨመሩም ነዉ የተዘገበዉ፡፡

የእስራኤል ጦር በቤካ ሸለቆ የሚገኘውን የሄዝቦላህ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ቦታዎችን በአንድ ጀምበር መምታቱን ተናግሯል።

የሊባኖስ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በዚህ ጥቃት አንድ ሰው ህይወቱ እንዳለፈና ተጨማሪ 30 ሰዎች መቁሰላቸዉን አስታዉቋል፡፡

በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላህ በሰጠው ምላሽም በጎላን የሚገኙ የእስራኤል ወታደራዊ ቦታዎችን የሮኬት ጥቃት ኢላማ አድርጌያለሁ ብሏል።

በተጨማሪም የፍልስጤሙ ፋታህ ንቅናቄ እስራኤል በሊባኖስ የትጥቅ ክንፍ አባል የሆነዉን ግለሰብ ቀጣናዊ ግጭት ለመቀስቀስ ስትል ገድላለች ሲል ከሷል፡፡

በእስራኤል እና በሄዝቦላህ መካከል የድንበር ተሻጋሪ ጦርነት እንዲባባስ ምክንያት የሆነው የጋዛ ጦርነት ከጀመረ በኋላ በፋታህ አባል ላይ የደረሰ የመጀመሪያው ጥቃት ነበርም ተብሏል።

ሄዝቦላህ በጎላን ተራራማ ቦታዎች በሮኬት ጥቃት 12 ህጻናትን መግደሉን ተከትሎ እስራኤል በቤሩት የቡድኑን ከፍተኛ አዛዥ ከገደለች በኋላ ውጥረቱ እየጨመረ መምጣቱ ተገልጿል፡፡

እስካሁን በሊባኖስ ከ5መቶ30 በላይ ሰዎች መሞታቸው የተዘገበ ሲሆን፤ከነዚህም ውስጥ ቢያንስ 130 የሚሆኑት ንፁሀን ዜጎች ናቸዉ ተብሏል፡፡

በተጨማሪም በሁለቱም በኩል ድንበር ላይ ወደ 2 መቶ ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ተፈናቅለዋል ሲል የዘገበዉ ቢቢሲ ነዉ፡፡

በሊዲያ ደሳለኝ

ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *