ከጅቡቲ ወደ ተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እየተጓጓዘ ያለው የምግብ ዘይት የኑሮ ውድነትን ለማሻሻል ያለመ ነው፡፡
በተጨማሪም ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል የገበያ ዋጋን ለማረጋጋት ታስቦ በመንግሥት የተገዛ ነው፡፡
በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽንና የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ከኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ጋር በመቀናጀት ነው ዘይቱ ወደ ሀገር ውስጥ እየተጓጓዘ የሚገኘው፡፡
መረጃው ፡- በጅቡቲ የኢትዮያ ኤምባሲ ነው፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ነሐሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም
