ድርጅቱ በደንበኞች ንብረትና ህይወት ላይ ለደረሰ አደጋ እንዲሁም ከሕጋዊ ኃላፊነት ጋር ለተያያዙ የካሳ ጥያቄዎች በበጀት አመቱ ብር 2.8 ቢሊዮን ክፍያ መፈፀሙን ገልፀዋል
በዚህም ከዕቅዱ የ18.2 በመቶ ቅናሽ እና ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተከፈለው ጋር ሲነጻጸር የ13.8 ቅናሽ ያሳየ ነው ሲሉ የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ነፃነት ለሜሳ ተናግረዋል
ከተከፈለው የካሳ ክፍያ ውስጥ የጠቅላላ መድን ድርሻ ብር 2.7 ቢሊዮን ወይም 95.3 በመቶ ሲሆን የረጅም ጊዜ መድን ዘርፍ ብር 132 ሚሊዮን ወይም 4.7 በመቶ ድርሻ ይይዛልም ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የጉዳት ካሳ ምጣ 52.2 በመቶ ሲሆን ይህም ከዕቅዱም ከኢንዱስትሪው የጉዳት ካሳ ምጣኔ ሲነጻጸር ዝቅ ያለ እንደሆነም ተነግሯል
አቶ ነጻነት ድርጅቱ በ2016 በጀት ዓመት ከ1.66 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ከታክስ በፊት ማማስመዝገቡ ነግረውናል ፡፡
የተገኘው ውጤት ከተያዘው እቅድ ጋር ሲነጻጸር በ7.5 በመቶ እና ካለፈው በጀት ዓመት ውጤት ደግሞ በ15 በመቶ ዕድገት አሳይቷል ብለዋል ፡፡
በሃገሪቷ ማህበራዊ፤ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶች፤ ምክንያት በተለያዩ የሀገራችን አካባቢ በተለይም ደግሞ በሰሜኑ እና በምዕራቡ ኢትዮጵያ አካባቢ በሚገኙ ቅርንጫፎቻችን በበቂ ሁኔታ ስራ ለመስራት አለመቻሉንም ሀላፊው ጨምረው ተናግረዋል፡፡
ለዓለም አሰፋ
ነሐሴ 24 ቀን 2016 ዓ.ም
