ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ነሐኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ከኢትዮጵያ አንጋፋ ምሁራን አንዱ የሆኑትና በተለያዩ ሀላፊነቶች ሀገራቸውን ያገለገሉት ፕሮፌሰር አንድርያስ እሸቴ፤ በተማሪ ንቅናቄ ንቁ ተሳትፏቸው እና በብሄር መብት ተሟጋችነታቸው ይታወቃሉ።

ከኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት ዘመን ጀምሮ ሕገ መንግሥት በማርቀቅና በማማከር ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረጉት ፕሮፌሰር አንድርያስ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ፕሬዚዳንት ሆነው ከማገልገላቸው በተጨማሪ በተለያዩ የመንግሥት ሀላፊነቶች ሀገራቸውን አገልግለዋል።

ነሐሴ 23 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *