የሱማሊያ መንግስት የኢትዮጲያን ሉአላዊነት በሚፃረር መልኩ  ከሌሎች ሀገራት ጋር ማበሩን እንዲያቆም  ኢትዮጲያ አሳሰበች፡፡

በዛሬው እለት  ወቅታዊ ጉዳዮች  ዙሪያ  ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ  መግለጫ ሰተዋል፡፡

አምባሰደር ታዬ   በወቅታዊ የሀገሪቱ የውጭ ግንኙነቶች ላይ በማተኮርም የተለያዩ ሀሳቦችን  ያነሱ ሲሆን  ሀገሪቱ  ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት ሰላማዊ በሆነ መንገድ የማስቀጠል ፍላጎት እንዳላትም አስታውቀዋል፡፡

አምባሳደር ታዬ  ከሰሞኑን ከሱማሊያ መንግስት ጋር የተፈጠረው ውጥረት ተከትሎ  የሱማሊያ መንግስት በተለይ የኢትዮጲያን መከላከያ ሰራዊት ማመስገን እና ማክበር ሲገባው አሁን ላይ እያሳየ ያለው ምላሽ የሚወገዝ እና ተቀባይነት የሌለው ቢሆንም  ኢትዮጲያ ከሱማሊያ ጎን በመቆም በተለይ አልሸባብን ለመመከት የምታደርገውን ድጋፍ  አጠናክራ  ትቀጥልበታለች  ብለዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ   የሱማሊያ  መንግስት  ከሌሎች ሀገራት  ጋር በማበር  የኢትዮጲያን  ጥቅም የሚፀረሩ  አሉታዊ  ተግባራትን ማስተናገዱን እንዲያቆም ሲሉ አምባሳደር ታዬ  አሳስበዋል፡፡

ከቀናት በፊት  ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናን የማተራመስ እርምጃን በዝምታ እንደማትመለከተው  ኢትዮጲያ  ማሳወቋ ይታወሳል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ነሐሴ 24 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *