የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት  በ68 ሰራተኞቹ ላይ እርምጃ ወስጃለው አለ

የአገልግሎቱ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዮሀንስ ገብሬ ለጣቢያችን እንደተናገሩት በመዲናዋ በ2016  በጀት  ከደንበኞች  በሚደርሰው ቅሬታ መሰረት እንዲሁም  ተቋሙ በራሱ አጣራሁት ባለው መረጃ መሰረት  በስነምግባር ግድፈት ምክነያት 68 የሚጠጉ ሰራተኞቹ ላይ አርምጃ ተወስዷል ብለዋል፡፡

የስነምግባር ግድፈት ያለባቸውን ሰራተኞች በሁለት መንገድ    ለማጣራት የሞከሩ ሲሆን አንዱ ተቋሙ ባለው የማጥረታ ሂደት ሲሆን ሁለተኛው ደፍሞ ከደንበኞች በሚመጡ ቅሬታ መሰረት ነው ብለዋል፡፡

በዚህ ጠሰረት  20 የሚሆኑት ሰራተኞች  የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሲሆን   42 የሚጠጉት ደግሞ የደሞዝ ቅጣት እንደተላለፈባቸው በገለፁ ሲሆን  የተቀሩት 5ቱ ደግሞ ከስራ መባረራቸውን ተናግረዋል፡፡

እርምጃ ከተወሰደባቸው ሰራተኞች መካከል በከፍተኛ ደረጃ የሚገኙ አመራረሮች እንዳሉ የነገሩን ሃላፊው ጉዳያቸው በህግ የተያዘ እንዳለም ገልፀዋል፡፡

ሰራተኞቹ የተቋሙን ህግ እና መርህ ያላሟሉ እንዲሁም የተሰጣቸውን ስራ ሃለፊነት እና ግዴታቸውን ያለተወጡ  መሆናቸውን ሀላፊው ጨምረው ተናግረዋ፡፡

የአገልግሎቱ ደንበኞች ሰራተኞቻችን ላይ ቅሬታና እና የስነምግባር ጥሰት ካስተዋሉ  ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማሳወቅ እንደሚችሉም ጠቁመዋል።

በለዓለም አሰፋ

ነሐሴ 24 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *