አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በአዲሱ የትምህርት ዘመን መምህራንንም ሆነ  ተማሪዎችን የመምረጥ መብት እንዳገኘ ገለፀ።

የዩንቨርስቲው ተጠባበቂ ኘሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ዩንቨርስቲው  ከአዲሱ 2017 ጀምሮ ተቋማዊ ነፃነትን ማግኘቱን ተከትሎ መመሪያ መዘጋጀቱን አስታወቀዋል።

የተማሪዎች የቅበላ በተመለከተ ወደ ዩንቨርሲቲዉ ምደባ የማይደረግበት መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር ሳሙኤል ተማሪዎች ወደ ዩንቨርሲቲዉ ለመቀላቀል የሚያስችላቸዉ  የተዘጋጀ መስፈርት መኖሩንም ገልፀዋል።

ተማሪዎችን ለመቀበል የ12 ክፍል መልቀቂያ ፈተና 50 በመቶ በላይ መምጣትን  መስፈርት ከማድረግ ባለፈ ዩንቨርሲቲ ራሱ በሚያዘጋጀው የመግቢያ ፈተና ማለፍ ግዴታ መሆኑ ተነግሯል።

የተዘጋጀውን የመወዳደሪያ ነጥብ የመግቢያ ፈተና እንዲሁም ሌሎች መስፈርት ሲያሟሉ ብቻ ወደ ዩንቨርስቲዉ የሚገቡ ይሆናል ።

አዲሱ አሰራር በመንግሥት ወጪ የሚሸፈን የትምህርት እድል እና በግል ወጪን በመሸፈን የተማሪዎች ስብጥር እንዲደረግ ተደርጓ ተቀርጿል ተብሏል።

ዩንቨርስቲዉ በየአመቱ በቅድመ ምረቃ ትምህርት ክፍል ከ 5 ሺህ ተማሪዎችን በድህረ ምረቃ ደግሞ የአላፊ ተማሪዎችን ቁጥር ታሳቢ እንደሚደረግ ተገልፆል።

ቁምነገር አየለ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *