ኢሰመኮ በህግ ማስከበር እና በመንግሰት መዋቅር መላላት ሳቢያ የሰዎች እገታ መበራከቱን በምርመራ አረጋግጫለሁ አለ።

ተቋሙ ዛሬ ባወጣዉ የምርመራ መግለጫ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የተራዘመ ከትጥቅ ግጭቶች ጋር ተያይዞ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የታጣቂ ሀይሎች ÷ ለዘረፋ በተደራጁ ቡድኖች እንዲሁም በአንዳንድ አካባቢዎች  የፀጥታ ሀይሎች የሚፈፀሙ እገታዎች እየተበራከተ መሆኑን የምርመራ ዉጤቱ እንዳመለከተው አሳዉቋል።

በሁለቱ ክልሎች እገታን በተመለከተ የቀረቡለትን አቤቱታዎች መነሻ በማድረግ እና የሰብዓዊ መብት ክትትል በማድረግ ተጎጂዎች ÷ የተጎጂ ቤተሰቦቻቸውን ÷ እንዲሁም የመንግስት ሀላፊዎችን እና ምስክሮችን በማነጋገር ምርመራ ሲያደርግ መቆየቱን ገልፆል።

የምርመራ መግለጫው ያካተታቸዉ በርከት ያሉ የእገታ ጉዳዮች በማሳያነት ያቀረበ ሲሆን በተጨማሪም በተለያዩ ምክንያቶች ምርመራ እና ክትትላቸዉ ያልተጠናቀቀ የእገታ ጉዳዩችን ይፋ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

መንግሥት በጸጥታ አካላቱ አባላት ብቻ ሳይሆን የታጠቁ ቡድኖችን ጨምሮ በ3ኛ ወገኖች ከእገታ ጋር በተያያዘ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ለመከላከል እንዲሁም የአጥፊዎችን ተጠያቂነት እና የተጎጂዎችን ፍትሕ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ ውጤታማ እርምጃዎችን እንዲወስድ አሳስቧል።

የኢሰማኮ ተጠባባቂ ኮምሽነር ራኬብ መሰለ በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች አሳሳቢ ሆኖ ለቀጠለው የእገታ ተግባር ዘላቂ በሆነ መልኩ እልባት ለመስጠት ለሰዎች እገታ መነሻና አባባሽ ምክንያት የሆነውን የሰላም መደፍረስና የትጥቅ ግጭትን በዘላቂነት በሰላማዊ መንገድ መፍታትን ጨምሮ ውጤታማ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባል” ብለዋል።

ቁምነገር አየለ

ነሐሴ 28  ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *