ሩሲያ በሊቪቭ ላይ ባደረሰችው ጥቃት በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ቆስለዋል እንዲሁም ሕንፃዎች ላይ ጉዳት ደርሷል ነው የተባለው ።
የከተማው ከንቲባ እንደተናገሩት በዩክሬን ምዕራብ በሌቪቭ ከተማ ሶስት ህፃናትን ጨምሮ ሰባት ሰዎች ተገድለዋል ።
በዩክሬን ማዕከላዊ ከተማ ፖልታቫ በሚገኝ ወታደራዊ ተቋም ላይ ማክሰኞ ዕለት በደረሰ ጥቃት ሀምሳ ሰዎች ከተገደሉ በኋላ የተከሰተ አዲስ ጥቃት መሆኑም ተገልጿል።
የከተማዋ ከንቲባ አንድሪ ሳዶቪ እንደተናገሩት፤ሩሲያ ባለፈው ረቡዕ መጀመሪያ ላይ በሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሃይፐርሶኒክ ሚሳኤሎች ጥቃት አድርሳለች ብለዋል ።
ከተገደሉት መካከል አንድ ህጻን እና ሁለት የ9 እና የ14 አመት ሴት ልጆች እንዲሁም በከተማዋ በአዋላጅነት የምትሰራ ሴት እንደሚገኙበት ባለስልጣናት ተናግረዋል።
በጥቃቱ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መቁሰላቸውንና በከተማው መሃል ፣ ቤቶች ፣ ትምህርት ቤቶች እና ክሊኒኮችን ጨምሮ ከ50 በላይ ሕንፃዎች ተጎድተዋል ሲሉ ከንቲባው ለቢቢሲ ተናግረዋል ።
ሊዲያ ደሳለኝ
ነሐሴ 29 ቀን 2016 ዓ.ም
