በማዕከላዊ ኬንያ በአንድ የመጀመሪያ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤት ላይ በተነሳ እሳት 17 ተማሪዎች ሞቱ።

አደጋውን “አሰቃቂ እና አሳዛኝ” ብለው የገለጹት የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ፤ መንስዔው እንዲጣራ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

ትናንት ሐሙስ ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም. በማዕከላዊ ኬንያ ኜሪ ግዛት በሚገኘው ሂልሳይድ ኢንዳራሻ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የእሳት አደጋው እንዴት እንደተነሳ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን የፖሊስ ቃል አቀባይ ሬሲላ ኦንያንጎ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።

“ለእሳት አደጋው ተጠያቂ የሆኑ በሕግ ይጠየቃሉ” ሲሉ ፕሬዝዳንቱ በኤክስ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

በተነሳው ቃጠሎ ከሞቱት 17 ተማሪዎች በተጨማሪ ሌሎች 14 ተማሪዎች በቃጠሎ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ለሕክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የሀገሪቱ ፖሊስ ገልጿል።

በዚህም ምክንያት የሟቾች ቁጥር ሊጨመር እንደሚችል ተሰግቷል።

የእሳት አደጋውን መነሻ የሚያጣራ መርማሪ ቡድን አደጋው ወደደረሰበት ግዛት መጓዙን ፕሬዝዳንቱ ጨምረው ገልጸዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *