ሐማስ የጋዛ ጦርነት እንዲቆም አሜሪካ በእስራኤል ላይ በቂ ጫና አላደረገችም ሲል ወቀሰ

በጋዛ ያለው ጦርነት እንዲቆም አሜሪካ በእስራኤል ላይ በቂ ጫና አላደረገችም ሲል ሐማስ ወቀሰ።

በሌላ ዜና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በያዝነው ወር መጨረሻ ወደአሜሪካ ያቀናሉ ተብሏል።

የሐማስ ከፍተኛ የአመራር አባል የሆነው ኦሳማ ሐምዳን ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ በሰጠው ቃለምልልስ የጋዛ ጦርነትን ለማስቆም አሜሪካ በእስራኤል ላይ በቂ አልያም ተገቢ ጫና አልፈጠረችም ብሏል።

በአንጻሩ አሜሪካ እስራኤል ለምትፈጽማቸው ተግባራት ውግንና ታሳያለች አልያም ሽሽትን ትመርጣለች ሲልም ወቅሷል።

በሌላ ዜና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በመጪው መስከረም 24 ወደ ኒውዮርክ ያቀናሉ ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ4 ቀናት ቆይታቸው በኒውዮርክ በሚካሄደውና የተለያዩ የሐገራት መሪዎች ይገኙበታል በተባለው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉ ታውቋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 06 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *