እስራኤል  በሰሜናዊ  ግንባር ጦርነት ልትጀምር ነዉ

የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን  ኔታንያሁ አስተዳደር  በሄዝቦላህ ጥቃት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቄያቸዉ ለመመለስ በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል  ጦርነት  ሊጀምር ነዉ ተብሏል፡፡

በጋዛዉ ጦርነት ምክንያት ከሄዝቦላህ ጋር  የተኩስ ልዉዉጥ እያደረገች  የምትገኘዉ እስራኤል ከ60 ሺህ በላይ ዜጎቿ ከሰሜናዊ  ክፍል ተፈናቅለዉባታል፡፡

እናም እነዚህን ዜጎች ወደ መንደራቸዉ ለመመለስ  ከጋዛዉ ግንባር በተጨማሪ በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል ጦርነት  ለመጀመር  ማቀዷ ተሰምቷል፡፡

በኢራን እንደሚደገፍ የሚነገርለት  የሊባኖሱ ሄዝቦላህ  እስራኤል በጋዛ የምታደርሰዉን ጥቃት እስካለቆመች ድረስ ጥቃቱን እንደሚቀጥል በተደጋጋሚ  አስታዉቋል፡፡

ቴልአቪቭ በበኩሏ ሄዝቦላ ከድርጊቱ የማይቆጠብ ከሆነ ቡድኑን ብቻም ሳይሆን ሀገረ ሊባኖስን ወደ ድንጋይ ዘመን እንደምትመልስ ዝታለች፡፡

የእስራኤል የጦር አመራሮች  አሁን ላይ የሀገሪቱ ጦር  ከጋዛ ባሻገር  ትኩረቱን ወደ ሊባኖስ ድንበር እንዲያዞር እያሳሰቡ ይገኛሉ፡፡

ይህንንም ተከትሎ ቀጠናዊ ጦርነት  ይቀሰቃሳል የሚለዉ ስጋት አሁንም አይሏል፡፡

ልዑል ወልዴ

መስከረም 07 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *