የከሸፈው ሁለተኛ የግድያ ሙከራ የተደረገው ፍሎሪዳ በሚገኘው የዶናልድ ትራምፕ ጎልፍ መጫወቻ ሜዳ ውስጥ ተደብቆ በነበረው የ58 ዓመት ተጠርጣሪ ነበር
ተጠርጣሪው አጥር ስር ተደብቆ በቅርብ ርቀት ዶናልድ ትራምፕ ላይ ሲያነጣጥር የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጠባቂዎች (ሴክሬት ሰርቪስ) አባላት ተኩስ ተከፍቶበታል።
ወደ ተሽከርካሪው ሮጦ ለማምለጥ ቢሞክርም በቁጥጥር ሥር ውሏል። ራየን ዌስሊ ሩዝ የተባለው ተጠርጣሪ የጦር መሣሪያ አነጣጥሮ ዶናልድ ትራምፕን ይጠባበቅ እንደነበር የአሜሪካ ባለሥልጣናት ገልጠዋል
ሰውዬው ዌስት ፓልም በሚፈኘው የጎልፍ መጫወቻ ሥፍራ ምግብ እና መሣሪያ ይዞ ለ12 ሰዓታት ግድም መቆየቱ የጥበቃ ሁኔታው አሳሳቢ ነው አስብሏል ።
የቀድሞው ፕሬዚደንት ለምርጫ ዘመቻ ወደ ሚቺጋን ማቅናታቸው ተዘግቧል ።
የዴሞክራቲክ ፓርቲ ተወካይዩዋ ተቀናቃኛቸው ካማላ ሐሪስም በበኩላቸው ወደ ፔንሲልቫኒያ ለምርጫ እንዳቀኑ ተጠቅሷል ።
ዶናልድ ትራምፕ ላይ በሁለት ወራት ጊዜያት ግድም ሁለተኛ የመግደል ሙከራ መደረጉ ግን እጅግ አነጋግሯል ።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 07 ቀን 2017 ዓ.ም
