በፔሩ ከፍተኛ በሆነ የደን ቃጠሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታዉጇል።

በሀገሪቱ ሶስት ክልሎች ሳን ማርቲን ÷ ኡካሊያ÷ አማዞና ከፍተኛ የደን ቃጠሎ የሰደድ እሳት መከሰቱ ታዉቋል።

በዚህም አስራ ስድስት ያህል ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ከ መቶ አርባ በላይ ያህሉ ደግሞ መቁሰላቸዉን ተነግሯል።

ኘሬዚደንት ዲና ቦሉዋርቴ በነዚህ ሶስት ክልሎች አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸዉን አስታወቀዋል።

በእሳቱ ነበልባል ከ 5 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት መቃጠሉን ገልፀዉ እሳቱን ለማጥፋት አዉሮፕላኖች ለማስገባት ተቸግረናል ብለዋል።

የሀገሪቱ ለበርካታ ጊዜ ባስተናገደችው የከፋ ድርቅ ለደን ቃጠሎዉ ምክንያት ነዉ ሲሉ እየገለፁ ይገኛሉ።

ዘገባዉ የአናዶሉ ነዉ።

ቁምነገር አየለ

መስከረም 8 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *