ጉርሻ ሀብ የማህበራዊ ሚድያ ተፅእኖ ፈጣሪዎች እና የይዘት ፈጣሪዎች በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ
የይዘት ባለቤቶች ቋሚ ገቢ ማድረግ የሚያስችላቸው ቀጥተኛ የይዘት ገቢ መፍጠሪያ የድህረ-ገፅ መተግበሪያ ነው ተብሏል።
የመተግበሪያ አበልፃጊዎች ቀጥተኛ የይዘት ገቢ መፍጠሪያ የድረ-ገፅ መተግበሪያ መሆኑን በሰጡት መግለጫ መግለጫ ተገልጿል።
የይዘት ፈጣሪዎች እና አድናቂዎቻቸውን የድጋፍ እና የሸልማት ማጋራት መስተጋብር የሚያሳልጥ የክፍያ ስርአት ስላላዘጋጁ የተፈጠረ ትልቅ ክፍተት አለ ተብሏል
የጉርሻ ሀብ አበልፃጊዎች በዚህም የተነሳ የሀገራችን የማህበራዊ ሚዲያ እምርታ እና የተሰጥኦ ዝመና በአሉታዊ ተፅእኖዎች ስር ሲወድቅ ይስተዋላል ብለዋል።
በጉርሻ ሀብ የሚገኙ ፊውቸሮች Donations፣ Memberships፣ Digital Extras Shop፣ Crowdfunding፣ Partnerships ሲሆኑ የክፍያ ሂደቱም በቻፓ (Chapa) የክፍያ አማራጭ እንደሚከፈል ነው የተገለፀው።
አለም አቀፋዊ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በያዝነው አመት በምስራቅ አፍሪካ ሀገሮች ያለው አማካኝ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎችቁጥር በአማካኝ ከሀገሮቹ የህዝብ ቁጥር በ 12 በመቶ ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡
በአባቱ መረቀ
መስከረም 09 ቀን 2017 ዓ.ም
