ከኢትዮጵያ ረጃጅም ሰዎች ውስጥ አንዱ ለሆነው ነገዎ ጅማ መኪና ተበረከተለት።

ከኢትዮጵያ ረጃጅም ሰዎች ውስጥ አንዱ ለሆነው ነገዎ ጅማ በኦክሎክ ሞተርስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር መኪና ተበረከተለት።

ነገዎ ጂማ የመቂ ከተማ ነዋሪና እድሜው 24 ሲሆን2፡25 ሴሜትር ይረዝማል።

በማሀበራዊ ሚዲያ የምናውቀውና ቁመቱ 2.25 ሳ.ሜ ለሆነው ለአቶ ነገዎ ጂማ አቢሹ በቁመቱ መርዘም ምክንያት ሁልጊዜ በሚያጋጥመው የትራንስፖርት ችግር ምክንያት መፍትሄ እንዲሆነው ታስቦ ነው መኪናው የተበረከተለት ተብሏል ።

የአክሎክ ሞተርስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ባለቤት የሆኑት አቶ አህመዲኒ ሞሃመድ እንዳሉት ዛሬ ለአቶ ነገዎ ጂማ የተበረከተው መኪና ያለውን ቁመት ከግምት ውስጥ በማስገባት የተገጣጠመ ነው ብለዋል።

አቶ አህመዲን በተጨማሪም ከዛሬ ጀምረው ባሉት ለተከታታይ አምስት አመት አቶ ነገዎን ብራንድ አንባሳደር አድርገነዋል ብለዋል።

በዛሬው እለት የተበረከተው ተሽከርካሪ ዋጋው 4 ሚሊዮን ብር የሚገመትና ባለ 7 መቀመጫ ድርጂቱ ኪሚገጣጥመው የ2022 ዊሊንግ ኤስ ሞዴል መሀከል ነው፡፡

አቶ ነገዎ በበኩሉ ከዚህ በፊት በከተማ ከቦታ ቦታ ለመዘዋወር በቁመቱ ምክኒያ ችግር ሲያጋጥመው እንደነበር ተናግሮ ዛሬ በተሰጠው መኪና ከመንቀሳቀሻነት ባሻገር እራሴን በኢኮኖሚ ደግፍበታለሁ ብሏል።

ኦክሎክ ሞተርስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአዲስ አበባና በመቀሌ ከተማ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካዎችን ከፍቶ ሙሉ በሙሉና በከፊል የተበታተኑ የመኪና አካላትን ሀገር ውስጥ በማስመጣት የመገጣጠም ስራ ላይ ተሰማርቶ እየሰራ ያለ ድርጅት መሆኑ ተነግሯል።

በልዑል ወልዴ

መስከረም 09 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *