በአለም ላይ በአንድ አመት ውስጥ ከ1 ቢሊዮን በላይ ሰዎች በጉንፋን በሽታ እንደሚያዙ መረጃዎች ያሳያሉ።
በዚህ ህመም ማንኛውም ሰው ሊጠቃ እንደሚችልም ይነገራል፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከጣቢያችን ገር ቆይታ ያደረጉት ከአንገት በላይ ህክምና ስፔሻሊስት እና የመስማት ችግሮች ህክምና ልዩ ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ሚካኤል ከበደ ናቸው፡፡
ጉንፋን(common cold) ምንድን ነው?
ጉንፋን በቫይረስ ምክንያት የሚመጣ የቫይረስ ኢንፌክሽን ነው ይላሉ፡፡
በሽታው በብዛት አየር ቧንቧን የሚያጠቃ ሲሆን በተለይ ጉሮሮን አንዳንዴ ደግሞ የታችኛውን የአየር ቧንቧ እንደሚያጠቃ ይናገራሉ፡፡
ጉንፋን አብዛኛውን ጊዜ ቀዝቀዝ ባሉት ወራት የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነው ፡፡
ሰዎች ለጉንፋን መያዛቸው ዋናው መንስኤ ቫይረሶች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?
- ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ
- የጎሮሮ ህመም
- ሳል
- ማስነጠስ
- ሰውነት መቆረጣጠም
- በተወሰነ መልኩ ትኩሳት መኖር
- የአፍንጫ መታፈን
- የማሽተት አቅም መቀነስ እና ስንመገብ የምግብ ጣዕም መቀየር ሊኖር እንደሚችል ይናገራሉ፡፡
ምልክቶቹ በአብዛኛው ከ7 እስከ 10 ቀን ይቆያሉ፡፡
መፍትሄዎቹ ምንድን ናቸው?
- እረፍት ማድረግ
- በበቂ ሁኔታ ውሀ መጠጣት
- ምልክቶቹን ለመቀነስ የሚረዱ መድሀኒቶችን መውሰድ( snip,flustop)
ጉንፋን በሚይዘን ሰአት አንቲባዮቲክ መድሀኒቶችን መውሰድ ተገቢ አለመሆኑንም አንስተዋል፡፡
በመጨረሻም ምልክቶቹ ከ10 ቀን በላይ ከቆዩ፣ ህመሙ እየባሰ የሚሄድ ከሆነ፣ ለመተንፈስ ከተቸገርን እና የደረት ላይ ህመም የሚሰማን ከሆነ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ ተገቢውን ህክምና ማድረግ እንደሚያስፈለግ ዶ/ር ሚካኤል ተናግረዋል፡፡
በሐመረ ፍሬው
መስከረም 14 ቀን 2017 ዓ.ም
