በትግራይ የሚገኙ የኩላሊት ታማሚዎች የከፋ ችግር ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡

በትግራይ የኩላሊት ሕሙማን ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሃፍቶም አባዲ ለጣቢያችን እንደተናገሩት ህሙማኑ በመድሀኒት እንዲሁም በገንዘብ እጥረት ምክንያት የከፋ ችግር ላይ ይገኛሉ ብለዋል።

በትግራይ ብቸኛው ዲያሊሲስ ማድረጊያ ቦታ በአይደር ሆስፒታል እንደሆነ የነገሩን ሃላፊው ከ11 በላይ ማሽኖች ከዚህ ቀደም አገልግሎት ይሰጡ እንደበረ እና በአሁን ሰዓት አብዛኛው በእድሜ መግፋት ከጥቅም ውጭ እንደሆኑም ነግረውናል፡፡

በትግራይ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኃላ ወደ 40 የሚጠጉ ህሙማን አሁንም በአይደር እንደሚገኙ ያነሱት አቶ ሃፍቶም በዚህም ቁጥሩ በውል ባይታወቅም ወደ 10 የሚጠጉ ህሙማን በመድሃኒት እና በአቅም እጥረት ህይዋታቸውን እንዳጡም ጠቁመዋል፡፡

በክልሉ ለኩላሊት እጥበት እና ህክምና የሚያገለግሉ መድሃኒቶች በስፋት ባለመኖራቸው ምክንያት አዲስ አበባ እየመጡ እንደሚገዙ ያነሱት ሃላፊው በዚህም ለከባድ ወጪ እየተዳረጉ እንደሚገኙም ነግረውናል፡፡

እንደአጠቃላይ በትግራይ ምን ያህል ህሙማን ይገኛል የሚለውን መረጃው እንደሌላቸው የሚናገሩት አቶ ሃፍቶም ለዚህ ምክያቱም በክልሉ ለዚህ አገልግት የሚውለው ተቋም መቀለ አይደር ሆስፒታል ብቻ በመገኘቱ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ከፐሪቶሪያው ስምምነት በፊት ከ85 በላይ ህሙማን በመድሃኒት እና በመሰል ግብዓት እጥረቶች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

በለዓለም አሰፋ

መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *