በሊባኖስ ሄዝቦላህ ላይ ባነጣጠረው የእስራኤል የአየር ጥቃት ቢያንስ 492 ሰዎች መሞታቸውን የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገልጿል።
በዚህም ከ20 ዓመታት ወዲህ እጅግ አስከፊው ቀን ሆኖ ተመዝግቧል።
ሄዝቦላህ እአአ ከ2006 ወዲህ የገነባቸውን መሰረተ ልማቶችን ለማውደም የእስራኤል ጦር በወሰደው እርምጃ አንድ ሺህ 300 የቡድኑን ዒላማዎችን መምታቷን ገልጻለች።
በሺህዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦች ደግሞ ቤታቸውን ጥለው ተወሰደዋል።
ሄዝቦላህ በበኩሉ ከ250 በላይ ሮኬቶችን ወደ ሰሜናዊ እስራኤል ማስወንጨፉን አስታውቋል።
በስለታማ ነገሮች ሁለት ሰዎች መቁሰላቸውን የጤና ባለሙያዎች ተናግረዋል።
ሁለቱም ወገኖች ወደ ሁሉን አቀፍ ጦርነት እየተቃረቡ ባሉበት ወቅት የዓለም ኃያላን መንግሥታት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ሲያሳስቡ ቆይተዋል።
የሊባኖስ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከሟቾች መካከል 50 ህጻናት እና 58 ሴቶች መኖራቸውን እና ሌሎች 1,835 ሰዎች ቆስለዋል ብሏል።
ከሟቾቹ መካከል ምን ያህሉ ሲቪሎች እና ታጣቂዎች እንደሆኑ አልገለጸም።
በጥቃቱ ምክንያት በሺህዎች የሚቆጠሩ ቤተሰቦችም መፈናቀላቸውን የጤና ጥበቃ ሚንስትሩ ፍራስ አቢያድ ተናግረዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
መስከረም 14 ቀን 2017 ዓ.ም
