በቀጣናዊ ውጥረት ምክንያት ከስዊዝ ካናል ከምታገኘው ገቢ ከ6 ቢሊየን ዶላር በላይ ማጣቷን ግብፅ አስታወቀች።

የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አልሲሲ እንደተናገሩት ፤ በቀጣናው እየበረታ የመጣው ውጥረት አገራቸው ከስዊዝ ካናል ማግኘት ከሚገባት ገቢ ከ6 ቢሊየን ዶላር በላይ ማጣቷን ገልጸዋል።

እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለፃ ባለፉት 8 ወራት ጊዜ ውስጥ ገቢው ከ50 እስከ 60 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።

ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው ያሉብንን ችግሮች አገራችንን በማይጎዳ ፣በቀጣናው መረጋጋትን ማስፈን በሚችል እና ደህንነታችንንም ስጋት ውስጥ የሚከቱ ጉዳዮች ላይ ባለመሳተፍ ለመፍታት እንሞክራለን ብለዋል።

አሁን በቀጣናው ያለው ውጥረት ግጭቱን ሊያባብሰው እንደሚችልም አስጠንቅቀዋል።

የስዊዝ ካናል ለአለም ዓቀፍ ንግድ ወሳኝ የሆነ በአውሮፓ እና ኤስያ መካከል የሚገኝ አጭር የመርከብ መስመር ሲሆን፤ ለግብፅም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኝ ነው።

አናዶሉ

በእስከዳር ግርማ

መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *