ሌላ ጥፋትበመካከለኛዉ ምስራቅ!

አፋቸዉ ያሞጠሞጠ የዘመኑ ዉጤት የሆኑ የእስራኤል አነፍናፊ የጦር ጄቶች በሊባኖስ ሰማይ እሳት መትፋታቸዉን ቀጥለዋል፡፡

የእግረኛ ወታደሮቿመ የሊባኖሰን ድንበር ጥሰዉ ገብተዋል፡፡
ሊባኖስ ተወራለች

ሄዝቦላህም እስራኤል ላይ ሮኬት መተኮሱን እንደቀተለ ነዉ፡፡

ግድያዉ፣ ጥፋቱ፣ ዉድመቱ አሳዛኝ፣ አስጊ፣አሳሳቢና አስጨናቂም ሆኖ እንደቀቐጠለ ነዉ
መከከለኛዉ ምሥራቅ ዉድመትና ሞት ሱስ የሆነበት ቀጠና፡፡

የዚያች ምድር ብቻም ሳትሆን ንጹሃን በቦምብ ይነፍራሉ፡፡

የታደሉት ቤት ንብረታቸዉን ጥለዉ ህይዎታቸዉን ለማትረፍ በቤሩት ጎዳና ይቅበዘበዛሉ፡፡
በመሪር ሃዘን የተዋጠዉ የሊባኖሱ ሄዝቦላህም የእስራኤልን ሰማይ እያረሰ ሮኬቶችን ማዝነቡን ተያይዞታል፡፡

ከአረቡ አብዮት ድቁሳት፤ከሃያላኖቹ የእጅ አዙር ጦርነት፤ ከሁቲና ከሀገሬዉ መንግስት እልቂት ማገገም የተሳናት ሀገረ የመንም እንደ ልማዷ አል ኢሳንና ሆዳይዳ የተሰኙ ከተሞቿ በእስራኤል የጦር ጄቶች ነደዉባታል፡፡

የኢራን ፉከራና ጠመንጃ ዉልወላም ከምንጊዜዉም በላይ ከፍ ያለበት ወቅት ሆኗል፡፡

ዛሬ በአንድ አመቱ ጦርነት ወደ ምድረ በዳነት የተለወጠችዉ የጋዛ ምድር ብቻም ሳትሆን፤ ቤሩትም፤ ሰነዓም ቴል አቪቭም፤ ቴህራንም፤ ደማስቆም፤ ባግዳድም፤ አማንም፤ ረማላህም እንቅልፍ ከራቃቸዉ ቀናት ተቆጥረዋል፡፡

መሪዎቻቸዉም ከሄዝቦላዉ መሪ ሀሰን ናስራላህ ሞት በኋላ ልባቸዉ በፍርሃት ርዶ በየጥጋጥጉና በየዋሻዉ እስከመደበቅ መድረሳቸዉ ተሰምቷል፡፡

በተለይም ደግሞ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጠላቶቻችን ሆይ የትም ቦታ ብትወሸቁ ከኢላማችን ዉጭ አትሆኑም ማለታቸዉን ተከትሎ የሄዝቦላ መሪዎች ብቻም ሳይሆኑ የኢራኑ ሃይማኖታዊ መሪ አዛዉንቱ አያቶላህ አሊ ካሚኒም ወደ ድብቅ ቦታ መወሰዳቸዉ ታወቋል፡፡

ይህ ሁሉ የጋዛዉ ጦርነት የወለደዉ የመካከለኛዉ ምስረቅ አስጨናቂ ሁኔታ ነዉ፡፡

የእስራኤል ጦር የሃማሱን መሪ በሀገረ ሊባኖሰ መግደሉን አረጋግጧል፡፡

ፋታህ ሼሪፍ በሊባኖስ የሃማስ ቢሮ ዋና ሃላፊ የነበረ ሲሆን እሱም የእነሃሰን ናስራላህን ፅዋን ተጎንጭቷል፡፡
የአይሁዶች መጠነ ሰፊ ጥቃትም ፋርሶቹን ከእንቅልፋቸዉ እያባነነ ሰላም ነስቷቸዋል፡፡

የኢራኑ ፕሬዝዳንት መሱድ ፔዝሽኪያን አስተዳደርም የሀገረ እስራኤል ህልዉና እየጨለመነዉ በማለቱ የመካከለኛዉ ምስረቅን ቀጠናን ቤንዚን አርከፍኮበታል፡፡

ለመሆኑ የእስራኤል ጥቃጥና ዉድመት በቀጠናዉ እስከአፍንጫቸዉ ታጥቀዉ የሚገኙ ሃይሎችና የአረብ አለም መልስ ምን ይሆን የሚለዉ የብዙዎች ጥያቄ ነዉ፡፡

የሄዝቦላህ ወታደራዊ ዕዝ ክፉኛ እየተጎዳ ይመስላል። ነባር ከሚባሉት አዛዠች ግማሽ ያህሉ ተገድለዋል።

ፔጀርስ እና ዎኪ ቶኪ በተባሉት የግንኙነት መሣሪያዎች የደረሰው አደጋ የቡድኑን ሰንሰለት የበጣጠሰ ነው። አብዛኛው የጦር መሣሪያ ክምቹትም በእስራአተል አየር ድብደባ ከጥቅም ውጪ ሆኗል።

የመካከለኛው ምሥራቅ ፀጥታ ተንታኝ ሞሐመድ አል-ባሻ የናስራላህ መገደል ቡድኑ ላይ የሚያደርሰው ኪሳራ ከፍተኛ ነው ይላሉ።

ግድያው ቡድኑን ከጥቅም ውጪ የማድረግ አቅም ያለው፤ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ክንፉን የሚያፈራርስ ሊሆን” እንደሚችል ይተነትናሉ።

ነገር ግን ይህ ፀረ-እስራኤል የሆነ ቡድን ሙሉ በመሉ ከጥቅም ውጪ ይሆናል አሊያም ከእስራኤል ጋር ለሚደረግ የሰላም ድርድር ይቀመጣል ብሎ መጠበቅ የማይታሰብ እንደሆነ ያስረዳሉ።

የእራኤል የመከላከያ ኃይል አሊያም አይዲኤፍ ወታደሮች በእስራኤል እና ሊባኖስ ድንበር አቅራቢያ ልምምድ ሲያደርጉ የሚያሳይ ምሥል ወጥቷል።

የልምምዱ ዓላማ ወደ ሊባኖስ ለመግባት ነዉ፡፡

ነገር ግን ሄዝቦላህ ያለፉትን 18 ዓመታት በተለይ ደግሞ ካለፈው የሁለቱ አገራት ጦርነት ማብቂያ ጀምሮ ለሚመጣው ጦርነት ሲዘጋጅ ነበር።

ናስራላህ ከመገደላቸው በፊት ባደረጉት ንግግር የእስራኤል ጦር ወደ ደቡብ ሊባኖስ ዘልቆ ከገባ “ታሪካዊ ዕድል ይፈጠራል ሲሉ ለተከታዮቻቸው ተናግረው ነበር።

የእስራኤል ጦር ወደ ሊባኖስ መግባት ላይከብደው ይችላል። ነገር ግን ተመልሶ ለመውጣት ወራት እንደሚፈጅበት ይገመታል።

ለዛም ነዉ የሄዝቦላዉ ምክትል ናኢም ቃሲም እግረኛ ጦራችን በጥሩ ቁመና ላይ ይገኛል ማለታቸዉ ይላል የአልጄዚራ ዘገባ፡፡

አለም የጋዛዉ እልቂት እንዲያባራ ጩኽቱን ቢያሰማም ኢራንና የአረቡ አለም እስራኤልን ቢያስጠነቅቁም፤ የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታዉ ምክር ቤት በልምምጫም በማሳሰቢያም እስራኤልን ቢማጸንም የቤተ አግዮን አለቆች ግን አሻፈረኝ ማለታቸዉን ቀጥለዋል፡፡
ይባስ ብሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔተንያሁ በመንግስታቱ ድርጅት አትሮኖስ ላይ ቆመዉ በመጽሃፍ ቅዱስ ላይ የሰፈረዉን የንጉስ ሰለሞንን ከጸሓይ በታች አዲስ ነገር የሚለዉን ቃል ወስደዉ ደርጅቱ መፍትሄ እንዳልሰጣቸዉ ሸንቆጠ አድርገዉታል፡፡

ኔታንያሁ ሃማስንም ሄዝቦላህንም ኢራንም መግጠም ከፈለገች ላናሸንፍ የምንጀምረዉ ጦርነት አይኖረም ሲሉ እቅጩን ተናግረዋል፡፡

በመካከለኛው ምስራቅ የምርምር ተቋም ከፍተኛ ተመራማሪዉ ሚስተር ከሃሊድ ኤልጂንዲይ እስራኤል በተጨባጭ ጫና ሊፈጥሩ ከሚችሉ እርምጃዎች ውጭ፤ ለየትኛውም ውግዘትና ጩኸት ደንታ የላትም ብለዋል።

በእስራኤል ላይ ተጨባጭ እርምጃ ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ውግዘትና ወቀሳ ለውጥ አያመጣም።

በጋዛ ላይ እይወሰደች ባለው እርምጃ ብዙ ክስና ወቀሳ ድርሶባታል ግን አላቆመችም።
ስለዚህ በወቀሳና ውግዘት ብቻ እስራኤል ላይ ለውጥ ማምጣት አይቻልም።

ኢስራኤልን የሚያሳስባት ብቸኛው እርምጃ የጦር መሳሪያ እቀባ ብቻ ነው በማለት ከዚያ በመለስ ያለው ሁሉ ግን ባዶ ጩኸ ትነው የሚሆነው ብለዋል ።

የእስራኤሉ የስለላ ተቋም ሞሳድ እየረቀቀ መሄዱ ደግሞ ብዙዎች ጥላሞታቸዉን እንኳን ለማመን እንዲቸገሩ አድርጓቸዋል፡፡

ለዛም ነዉ ተንታኖጭ ከሁሉም በላይ ኢራናዊያን እንቅልፍ አልባ ሌሊቶችን እንዲያሳልፉ የሚያደርጋቸው የሞሳድ ኃያልነት ነው የሚሉት።

የትኛውም የኢራን ባለሥልጣን ከእስራኤል ዕይታ ውጭ አይደለም። አያቶላህም ቢሆኑ።
ለዛም ነዉ ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታ እንዲሸሸጉ የተደረጉት ተብሏል፡፡

ኔታንያሁ ግን የመጽሃፈ ሳሙኤልን ጥቀስ አጣቀሰዉ “የእስራኤል ዘላለማዊነት አይሻክርም” ዘመቻችንም ይቀጥላል ማለታቸዉ ብዙዎችን አስግቷል፡፡

ታዲያ በጋዛና በቤይሩት የሚቀጠፉትን ንፁኃን ማን ይድረስላቸዉ፡፡

ከ1948 ጀመሮ የተፈራረቁ ዲፕሎማቶች ተንታኞች አዋቂዎች እንደሚሉት በዚያ ምድር ሰላም እንዲወርድ የሚፈልግ ካለ ሠላም የሚገኘዉ በድርድር ብቻ ነዉ።

الله يحفظنا
/allah yahfazuna ይህ የሊባኖሳዉያን የወቅቱ ተማጽኖ ነዉ፡፡
ፈጣሪ ሆይ አድነን እንደማለት ነዉ በአረብኛ፡፡

በአባቱ መረቀ

መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *