በታይላንድ ዋና ከተማ ከባንኮክ ወጣ ብሎ በሚገኝ አካባቢ በደርዘን የሚቆጠሩ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ ተከስክሶ በእሳት መጋየቱ ተገልጿል ፡፡
16 ህጻናት እና ሶስት መምህራን ማምለጣቸው የተነገረ ሲሆን 22 ተማሪዎች እና 3 መምህራን ግን የደረሱበት አልታወቀም ሲሉ የሀገሪቱ የትራንስፖርት ሚኒስትር ተናግረዋል።
በሰሜናዊው የኡታይ ታኒ ግዛት ከትምህርት ቤት የመስክ ጉብኝት ተማሪዎችን እና መመህራንን ጭነው ሲመለሱ ከነበሩት ሦስት አውቶቡሶች አንዱ እንደነበር ነው የተነገረው።
አንድ የነፍስ አድን ሰራተኛ ለአካባቢው ቴሊቪዥን እንደተናገሩት አውቶቡሱ ወደ ባንኮክ በሚወስደው አውራ ጎዳና ላይ ሲጓዝ ጎማው ፈንድቶ መከስከሱን ገልፀዋል።
የታይላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር በበኩላቸው የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን መግለፃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በሐመረ ፍሬው
መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ.ም
