ይህ “የሚልየነሮች መንገድ” የተሰኘውን ስልጠና በበይነ መረብ እና በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ራዲዮ ለማሰራጨት የበላይ አትክልትና አስቤዛ ማዕከል በዛሬው እለት ስምምነት አድርገዋል፡፡
በርካታ ወጣቶች ስራ አጥ በሆኑባት ሀገር እና ምን ልስራ ብለው ግራ በተጋቡበት በዚህ ወቅት እንዲህ አይነት ይዘቶች ለህዝቡ መቅረባቸው የሚበረታታ ነው ብለዋል የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ራዲዮ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ መሰለ ገ/ህይወት ፡፡
የኢትዮጵያውያን የሆነው ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ለሀገር፣ለትውልድ የሚጠቅም በመሆኑ አስፈላጊው እገዛ ያደርጋል ብለዋል።
የፕሮግራሙ አላማ ግለሰዎች ባሉበት ሆነው የህይወታቸውን ግብ መምታት እንዲችሉና ‹‹የአይቻልምን ስብዕናን›› ወደ ‹‹ ይቻላል ›› መንፈሰ መቀየር ነው ያሉት የበላይ አስቤዛና አትክልት የንግድ ድርጅት መስራች እና ስራ አስኪያጅ አቶ በላይ ሞሪድ ።”የሚሊየነሮች መንገድ ለመከተል ያለን ነገር በቂ ነው”ብለዋል፡፡
ይህ ማዕከል ከዚህ ልምድ በመነሳት በቀጣይ ሁለት ዓመታት ውስጥ ብቻ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ዜጎችን በተግባርና በተጨባጭ ወደ ሚሊየነርነት የሚቀይር በልምድ የተረጋገጠ «የሚኒየነሮች መንገድ» የተሰኘ ፕሮጀክት በመንደፍ የቢዝነስ ፕላን በማዘጋጀት ለወጣቶች ፣ ለጀማሪ ነጋዴዎች እና በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርተዉ ያሉ አምራችና አከፋፋዮች ሲጠቀሙበት የሥራ አጥ ቁጥርን በመቀነስ የስራ ባህላችንን ይበልጥ የሚያሳድግ ፕሮጀክት ላይ ኢንቨስት እያደረገ እንደሚገኝ ተነግሯል።
በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢች 5 ትላልቅ ድርጅቶች ከፍተን ከ70 ሺህ በላይ ደንበኛ አፍርተናል ለበርካታ ሰራተኞች የስራ እድል ፍጥረናል ብለዋል አቶ በላይ ሞሪድ፡፡
ይህ ፕሮግራም በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ዘወትር ቅዳሜ ከቀኑ 10 ሰዓት እስከ 12 ሰዓት ለሁለት ሰዓት የሚተላለፍ ሲሆን ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ .ም ጀምሮ ስርጭት ይጀምራል ተብሏል ።
ለአካል ጉዳተኞች፣ መስማትና ማየት ለተሳናቸው ግለሰዎች ስልጠናውን ሊከታተሉበት የሚችሉበት አማራጭ መዘጋጀቱ ተገልጻል፡፡
በስልጠናው ለመሳተፍ እንዴት መመዝገብ ይቻላል እና በምን አማራጭ የሚለው በቅርቡ እናሳውቃለን ብለዋል፡፡
ልኡል ወልዴ
ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም
