የሐማስ መሪ ሲንዋር መገደሉን እስራኤል አሳወቀች
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሃማስ መሪ ያህያ ሲንዋር በጋዛ መገደሉን ተናግረዋል።
የሐማስ መሪ ዛሬ በእስራኤል ወታደሮች ተገድሏል ካሉ በኃላ ጥቅምት 7 ቀን ለተፈጸመው ጭፍጨፋ ዋና መሪ ሲሉም ገልፀውታል።
ካትዝ አያይዘውም “ይህ ለእስራኤል ጉልህ የሆነ ወታደራዊ እና የሞራል ስኬት እና መላው የነፃው አለም ትልቅ ድል ነው ብለዋል።
“የሲንዋርን መገደል ታጋቾቹ በአስቸኳይ እንዲፈቱ እድል ይከፍታል እናም በጋዛ ውስጥ አዲስ የውጥ መንገድ ይከፍታል – ያለ ሃማስ እና ያለ ኢራን ቁጥጥር”ነው ያሉት።
ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም
