ቤልጂየማዊው ግብ ጠባቂ ቲቧ ኩርቱዋ በተደረገለት ምርመራ ትላንት ምሽት ጉዳት እንዳጋጠመው መረጋገጡን ክለቡ አሳውቋል።
ኩርቱዋ ያጋጠመው ጉዳት ለሳምንታት ከሜዳ ሊያርቀው እንደሚችል ተዘግቧል።
ሎስ ብላንኮዎቹ በኤል ክላሲኮ ጨዋታ አንድሬ ሉኒንን በግብ ጠባቂነት የሚጠቀሙ ይሆናል።
ሌላኛው ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሮድሪግ በትላንት ምሽቱ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ጉዳት እንዳጋጠመው በህክምና ምርመራ መረጋገጡ ተገልጿል።
ይህንንም ተከትሎ ሮድሪጎ ሪያል ማድሪድ ከቀናት በኋላ ከባርሴሎና ጋር የሚያደርገው ተጠባቂው የኤል ክላሲኮ ጨዋታ የሚያመልጠው ይሆናል።
ተጠባቂው የኤል ክላሲኮ ፍልሚያ ቅዳሜ ምሽት 4:00 ሰዓት በሳንቲያጎ በርናቦ ስታዲየም የሚደረግ ይሆናል።
ጋዲሳ መገርሳ
ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ.ም
