ጤና ሚኒስቴር ለክልሎች፣ ለከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ፣ ለተጠሪ ተቋማትና ለሆስፒታሎች የተሽከርካሪ ድጋፍ ርክክብ አካሄደ

ጤና ሚኒስቴር ለክልሎች፣ ለከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ፣ ለተጠሪ ተቋማትና ለሆስፒታሎች የጤና አገልግሎት የሚውሉ አምቡላንሶችን ጨምሮ 260 ተሽከርካሪዎችን፣ 572 ሞተር ብስክሌቶችን፣ 2 ሺህ 700 ኮምፒዩተሮችን እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ክሊኒክ ድጋፍ አድርጓል።

የጤና ሚኒስትር ሚንስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በዝግጅቱ ላይ በመገኘት ለተቋማቱ የሥራ ኃላፊዎች የተሽከርካሪ እና የህክምና ቁሳቁስ ርክክብ አካሂደዋል

የጤና ሚኒስትሮ በዝግጂቱ ላይ እንደገለጹት፥ የዜጎችን ጤንነት በዘላቂነት ለማስጠበቅ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀዋል

የዛሬው የተሽከርካሪ እና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍም የጤና ተቋማት የዜጎችን ጤንነት ለማስጠበቅ የሚያደርጉትን ጥረት የሚያጎለብት መሆኑንም አነስተዋል።

አቤል እሰጤፋኖስ

ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *