የጀርመን መራኄ መንግሥት ኦላፍ ሾልስ ለዶናልድ ትራምፕ “የእንኳን ደስ አለዎ” መልዕክት አስተላልፈው ሀገራቸው ከአትላንቲክ ውቅያኖስ ባሻገር ለሚገኙት ለሁለቱም ነጻነት እና ብልጽግና ለመፍጠር ከአሜሪካ ጋር መሥራቷን እንደምትቀጥል አስታውቀዋል።
የአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኡርሱላ ፎን ዴር ላየን ትራምፕ በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎ መልካም ምኞታቸውን በኤክስ በኩል ገልጸዋል።
“የአውሮፓ ኅብረት እና አሜሪካ ከአጋር በላይ ናቸው። 800 ሚሊዮን ዜጎቻችንን አንድ በሚያደርግ እውነተኛ የሕዝቦች አጋርነት የተሳሰርን ነን” ብለዋል።
አውሮፓ እና አሜሪካ “ዘላቂ ኅብረት እና ታሪካዊ ትሥሥር እንዳላቸው የገለጹት የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ቻርለስ ሚሼል ተመሳሳይ የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፈዋል።
ትራምፕን “እንኳን ደስ አለዎ” ያሉት የዩክሬን ፕሬዝደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ የሩሲያ ጦርነት በዩክሬን ያበቃል የሚል ተስፋቸውን አያይዘው ገልጸዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም
