ከባዕድ ነገር ጋር የተቀላለቀሉ እና ህገወጥ የምግብ ምርቶችን ለመለየት በተሰራ የቁጥጥር ስራ ከ252 ሺ ኪግ በላይ ወይም ከ54.9 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ምርት ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡
በተለያዩ የምግብ ምርቶች ላይ፣ በምግብ ገበያ ማዕከላት እና የምግብ ችርቻሮ ድርጅቶች ላይ እንዲሁም በተለዩ የምግብ ዓይነቶች ላይ በ10 ዙር ቁጥጥር መካሄዱን ጣቢያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡
ቁጥጥሩ ከተደረገባቸው የምግብ አይነቶች ውስጥ የዱቄት ወተት፣ የምግብ ዘይት፣ የበቆሎ ዱቄት፣ የጤፍ ዱቄት፣የለውዝ ቅቤና ፕላምፕኔት ዋናዎቹ መሆናቸው ተገልጸል፡፡
የቁጥጥር ስራው ከተካሄዳባቸው አካባቢዎች መካከል ደግሞ ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣አዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ ተጠቃሽ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
የቁጥጥር ስራው የባለስልጣኑ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በተጠቀሱት አካባቢዎች ከሚገኙ የጤና ተቆጣጣሪ አካላት ጋር በጋራ በመሆን የተሰራ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
ሐመረ ፍሬው
ኀዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም
