የኢንተርፕርነር ልማት ኢንሲቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ ቦሩ ሸና፤ወጣቶች የሚያመጧቸውን የሥራ ፈጠራ ሀሳቦች ማስተናገድ የሚችል የፖሊሲ ስርዓት መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል።
በወጣቶች የሚመጡ የሥራ ፈጠራ ሀሳቦች ኢኮኖሚውን መደገፍ ወደሚያስችል አቅም እንዲያድጉ ለማድረግ የሥራ ፈጠራዎቻቸውን የሚያግዝ መሰረት መጣል ያስፈልጋል ነው ያሉት።
በመሆኑ በሁሉም ዘርፎች የተሰማሩ ወጣቶች የሚያመጧቸውን ሀሳቦች ማስተናገድ የሚችል የፖሊሲ ስርዓት መገንባት ያስፈልጋል ሲሉ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።
አቶ ቦሮ ፤የወጣቶችን ሀሳብ በመቀበል ለሥራ ፈጣሪዎችና አዳዲስ ሀሳቦቻቸው ምቹ ሥነ-ምህርዳር መፍጠር ያስፈልጋልም ብለዋል።
ሀገሪቷ ባላት አቅም የሥራ ፈጠራን ለመደገፍና ለማበረታታት ጥረት እየተደረገ መሆኑም ያነሱት ዳይሬክተሩ፤ ሁለንተናዊ ድጋፎችንና የፖሊሲ ማዕቀፎችን በማመቻቸት የሐብት ምንጭ ለማድረግ የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ መውሰድ ይገባልም ነው ያሉት።
ልዑል ወልዴ
ኀዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም
