ባንኩ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 940.7 ሚሊየን ብር ማትረፍ መቻሉን እና
ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀርም የ26 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን አስታውቋል።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በሒሳብ ዓመቱ 5.4 ቢሊየን ብር ብድር መሰጠቱን እና ተመሳሳይ መጠን ያለው ከብድር ተመላሽ ገንዘብ ማሰባሰብ መቻሉ ተጠቅሷል።
የባንኩ የተከፈለ ካፒታል ዓቅም 3.1 ቢሊዮን ብር መድረሱ እና አጠቃላይ ሀብትም 43.1 ቢሊዮን ብር መሆኑን ጣቢያችን ሰምቷል።
በሒሳብ ዓመቱ 8.3 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ገንዘብ በማሰባሰብ የባንኩ አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ 35.6 ቢሊዮን ብር ማድረስ ተችሏልም ተብሏል::
ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ310 ሺህ በላይ አዳዲስ የባንክ ሒሳቦችን በመክፈት የአስቀማጭ ደንበኞቹን ቁጥር ከሁለት ሚሊዮን በላይ ማድረሱን 20ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት አስታውቋል።
የዲጂታል እና የኤጀንት ባንኪንግ አገልግሎት ዘርፍ የተጠቃሚዎች ቁጥር ወደ 998,000 ከፍ ስለማለቱም ተነግሯል።
ተደራሽነት ከማሳደግ አንፃርም ባንኩ 18 አዳዲስ ቅርንጫፎችን ከፍቶ ለአገልግሎት በማብቃት እ.ኤ አ እስከ ሰኔ 30/2024 ድረስ አጠቃላይ የቅርንጫፎቹን ቁጥር ወደ 306 ማድረሱ ተነስቷል።
እንዲሁም 80 የገንዘብ መክፈያ ኤ.ቲ.ኤም ማሽኖችን በተለያዩ አካባቢዎች በመትከል የጥሬ ገንዘብ ፍሰት አገልግሎት ለማቀላጠፍ ጥረት እንደተደረገ ተገልጿል።
ባንኩ ለዜጎች የስራ ዕድል ከመፍጠር አኳያም በአጠቃላይ 6,365 ሰራተኞች እንዳሉት ተነግሯል።
ሐመረ ፍሬው
ኀዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም
