አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ ነጥብ ሲጥሉ ማንችስተር ዩናይትድ እና ቶተንሀም ሸንፈተ አስተናግዱ!
በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ መርሐግብር አርሰናል ከፉልሀም ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።
የፉልሀምን ግብ ሂምኔዝ ከመረብ ሲያሳርፍ ዊሊያም ሳሊባ አርሰናልን አቻ ማድረግ ችሏል።
አርሰናል በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው ያለፉት አራት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ የማዕዘን ምት ግብ ማስቆጠር ችሏል።
አርሰናል ካለፈው የውድድር ዘመን ወዲህ 23 ግቦችን ከቆመ ኳስ ማስቆጠር ችሏል ::
ማንችስተር ሲቲ ከ ክሪስታል ፓላስ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።
የማንችስተር ሲቲን ግብ ሀላንድ እና ሌዊስ ሲያስቆጥሩ
ለክሪስታል ፓላስ ሙኖዝ እና ላክሮይክስ ከመረብ አሳርፈዋል።
ማንችስተር ሲቲ በዚህ አመት በሰባት ጨዋታዎች በመጀመሪያዎቹ 15 ደቂቃዎች ግብ የተቆጠረበት ቀዳሚው ክለብ ሆኗል።
የማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጨዋች ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር ዘመኑ 13ኛ የፕርሚየር ሊግ ግቡን አስቆጥሮ።
ሲቲ በሁሉም ውድድሮች ባደረጋቸው ያለፉት ዘጠኝ ጨዋታዎች
21ግቦች ተቆጥረውበታል
6 ጨዋታዎች ተሸንፈዋል እንዲሁም
1 ጨዋታ አሸንፈው
2 አቻ ተለያይተዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።
የኖቲንግሀም ፎረስትን የማሸነፊያ ግቦች ሚሌንኮቪች ፣ ክሪስ ውድ እና ጊብስ ዋይት አስቆጥረዋል።
ቀያዮቹ ሴጣኖቹን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦች ሆይሉንድ እና ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከመረብ አሳርፈዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በውድድር ዘመኑ ስድስተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።
ኖቲንግሀም ፎረስት በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንችስተር ዩናይትድን በሊግ ጨዋታ ኦልድትራፎርድ ላይ አሸንፎታል።
ቼልሲ ከቶተንሀም ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 4ለ3 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
የሰማያዊዎቹን የድል ግቦች ኮል ፓልመር 2x ፣ ኢንዞ ፈርናንዴዝ እና ጄደን ሳንቾ ከመረብ አሳርፈዋል።
ቶተንሀምን ከሽንፈት ያልታደጉ ግቦች ዶምኒክ ሶላንኬ ፣ ሰን እና ኩሉሴቭስኪ አስቆጥረዋል።
ቼልሲ ማሸነፉን ተከትሎ ከሊጉ መሪ ሊቨርፑል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ማጥበብ ችለዋል።
ኮል ፓልመር አስራ ሁለት ተከታታይ ፍፁም ቅጣት ምቶችን በማስቆጠር በሊጉ አዲስ ታሪክ ፅፏል።
በሌሎች ጨዋታዎች
- አስቶን ቪላ ሳውዝሀምፕተንን 1ለ0
- ብሬንትፎርድ ኒውካስል ዩናይትድን 4ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል ።
- ሌስተር ሲቲ ከብራይተን 2ለ2 ሲለያዩ
- በርንማውዝ ኢፕስዊች ታውንን 2ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ከባድ አውሎ ንፋስ በመከሰቱ ምክንያት ሊደረግ የነበረው የመርሲሳይድ ደርቢ ኤቨርተን ከ ሊቨርፑል ጨዋታ ለሌላ ቀን ተላልፏል።
የሊግ ደረጃቸው
1 ሊቨርፑል :- 35 ነጥብ
2 ቼልሲ :- 31 ነጥብ
3 አርስናል:-29 ነጥብ
4 ማንችስተር ሲቲ :- 27 ነጥብ
5 ኖቲንግሀም ፎረስት :- 25 ነጥብ
11 ቶተንሀምን :- 20 ነጥብ
13 ማንችስትር ዩናይትድ:- 19 ነጥብ
ጋዲሳ መገርሳ
ኀዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም
