የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክክር ለማካሄድ ፍፁም ሰላም መሆን አለበት የሚል እምነት የለንም ሲል ገለፀ።
የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ይህን ምክክር ለማካሄድ በሀገሪቱ ያሉ ግጭቶች የግድ ሙሉ በሙሉ መቆም አለብት ብሎ ኮምሽኑ እንደማያምን ተናግረዋል።
አቶ ጥበቡ በሀገራችን ግጭቶች በስፋት እንዳሉ ቢታወቅም ምክክር ከማድረግ ግን አያግድም ብለዋል።
ምክክር በግጭት ጊዜ ይካሄዳል የሚሉት የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ በሌላ በኩል ፣ምክክር ግጭት ካለፈ በኋላም መካሄድ እንደሚችል የሌሎች ሀገራትን ልምድ ማየት ይቻላልም ብለዋል።
ኮሚሽኑ አሁንም የታጠቁ አካላት በምክክር ሂደቱ እንዲሳተፍ ጥረት እያደረገ ይገኛል፤ ሰላምን በማምጣት አሳታፊ የሆነ ምክክር ለማድረግ ቁርጠኛ ነው ሲሉም አቶ ጥበቡ ለጣቢያችን ተናግረዋል።
ለአለም አሰፋ
ኀዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም
